"ባህር ዳር ወደሚገኘው ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ሕክምና ፈልገው ከሚመጡ ታካሚዎች ውስጥ ከሕመማቸው በላይ የመድኃኒት ችግርና የምግብ እጥረት የሚያሰቃያቸው ታካሚዎች የሕክምና ባለሞያዎቹን ቀልብ ስበዋል" ይላል ተከታዩ ዘገባ።
የሕክምና ባለሞያዎቹ ከሚሰጡት የሕክምና አገልግሎት በተጨማሪ ለታካሚዎቹ አስፈላጊውን እርዳታ ለመስጠት "ፈውስ" የሚል የበጎ አድራጎት ማኅበር አቋቁመዋል።
ከወር ደሞዛቸው ከ10 እስከ 200 መቶ ብር ድረስ በማዋጣት ካሰባሰቡት ገንዘብ ላይ ችግረኛ ታካሚዎቹን ይረዳሉ። ሰሞኑን ወደ ሆስፒታሉ ጎራ ያለችው አስቴር ምስጋናው ተከታዩን ይዛለች።