በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በባሌ ድርቅ እንስሳት መሞት ጀምረዋል


በባሌ ድርቅ እንስሳት መሞት ጀምረዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00

በባሌ ድርቅ እንስሳት መሞት ጀምረዋል

በምስራቅ ባሌ ዞን በድርቅ ምክንያት እስካሁን ከ80 ሺ በላይ እንስሳት መሞታቸውን፤ ከ195 ሺ በላይ ደግሞ ካሉበት ለመነሳት በሰው የሚታገዙ መሆኑ ተገለፀ።

በዞኑ በተለይ ቆላማ አካባቢ ወረዳዎች ውስጥ የከብቶች መኖና ውሃ አለመኖሩ አሳሳቢ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገልጿል።

የምስራቅ ባሌ ዞን የአርብቶ አደረሮችና መስኖ ልማት ጽሕፈት ቤት የሰው ሕይወት ለመታደግ በተደረገው ርብርብ በድርቁ ምክንያት የሞተ ሰው የለም ሲል ገልጿል ።

የኦሮምያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ በዞኑ በመደበኛ እና በድርቅ ምክንያት ለረሀብ ለተጋለጡ ከ400 ሺ በላይ ሰዎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል። ድጋፍ እየተደረገ መሆኑኑንም ጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG