በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቡድን ፖላንድና ዩክሬን ላይ አለ


 አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን
አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን

በበርሊን የኢትዮጵያ ልዑክ ምክትል መሪ የሚመራ ቡድን ፖላንድና ዩክሬን ድንበር ላይ ተገኝቶ የዩክሬኑን ጦርነት እየሸሹ ድንበር ለሚያቋርጡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ፣ እንዲሁም የሌሎችም የአፍሪካ ሃገሮች ዜጎችና ለማንም እርዳት ለሚፈልግ ሰው ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን በርሊን የሚገኙት በጀርመን፣ በፖላንድ፣ በዩክሬን፣ በቼክ ሪፐብሊክና በስሎቫክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ዩክሬን ውስጥ የሚገኙትን ለመድረስ፣ የፖላንድን፣ የሃንጋሪን፣ የሮማንያን፣ የስሎቬንያን ድንበሮች እያቋረጡ የሚገቡት ደግሞ ማንኛውንም አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ቡድኑን እንዲያገኙ አምባሳደሯ አሳስበው የኃላፊዎቹን ቁጥሮች አካፍለዋል።

በዚህም መሠረት ፖላንድ ያለው ቡድን መሪ አምባሳደር ተፈሪ ታደሰን በስልክ ቁጥር +49 176 7269 0994፤ እንዲሁም በርሊን ያሉትን የዳያስፖራ ጉዳዮችና ኮንሱላር አገልግሎት ኃላፊ አቶ አስቻለው ከበደን በስልክ ቁጥር +49 176 8334 3348 እየደወሉ እንዲያገኙና ሃያ አራት ሰዓት ክፍት ሆነው እንደሚጠባበቁ አምባሳደር ሙሉ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ከዚህ ጋር የተያያዘውን ቃለ ምልልስ ካደረጉ በኋላ ድንበር መሻገሪያዎች ላይ በአፍሪካዊያን ላይ መድልዎ እንደሚደረግና በድንበሩ የዩክሬን በኩል አፍሪካዊያን ብቻቸውን ተሰብስበው እንዲቆዩ የሚደረግበት ካምፕ መሠራቱን የሚጠቁም መረጃ እንደደረሳቸው አምባሳደር ሙሉ አመልክተው “እንዲህ ያለ በቆዳ ቀለም ላይ የተመሠረተ አያያዝ ጨርሶ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል። ጉዳዩን ወደሚመለከታቸው ባለሥልጣናትና በርሊን ውስጥ ለሚገኙት የ48 የአፍሪካ ሃገሮች አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ቡድን መሪ እንደሚወስዱት ገልፀዋል።

ከአምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ብዙነህ ጋር የተደረገውን ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቡድን ፖላንድና ዩክሬን ላይ አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:20 0:00

XS
SM
MD
LG