በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከግማሽ በላይ የሚሆነው የአፍጋኒስታን ህዝብ ህይወት አድን ሰብዓዊ ርዳታ ያስፈልገዋል


ፋይል - በአፍጋኒስታን፣ ካቡል የሚገኝ ሆስፒታል በምግብ እጥረት የተጎዳ የ4-አመት ህፃን መሀመድን እግሮች እናቱ ይዛ ታሳያለች።  
ፋይል - በአፍጋኒስታን፣ ካቡል የሚገኝ ሆስፒታል በምግብ እጥረት የተጎዳ የ4-አመት ህፃን መሀመድን እግሮች እናቱ ይዛ ታሳያለች።  

ከ24 ሚሊየን በላይ ቁጥር ያለው፣ 59 ከመቶ የሚሆነው የአፍጋኒስታን ህዝብ በረሃብ ውስጥ እየኖረ መሆኑን፣ በዚህም ምክንያት ሰዎች ህይወታቸውን ለማቆየት ሲሉ ጠንካራ ርምጃዎችን እንዲወስዱ መገዳቸውን የሰብዓዊ ርዳታ ባለሙያዎች አስጠንቀዋል።

ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተውጣጡ ስምንት የአስቸኳይ ግዜ እርዳታ ባለሙያዎች ለአምስት ቀናት በአፍጋኒስታን ያካሄዱትን ተልዕኮ ሲያጠናቅቁ በሀገሪቱ ያስተዋሉት የሰዎች ስቃይ ግዙፍነት እጅግ እንዳስደነገጣቸው ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ እንዳሉት በርካታ አፍጋኒስታውያን ካለምንም ዓለም አቀፍ እርዳታ እየኖሩበት ያለውን እጅግ አስከፊ ሁኔታ መቋቋም አይችሉም። በመንግስታት ድርጅቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪትይ ቢሮ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው በዚህ አመት ለአፍጋኒስታን ርዳታ ከተጠየቀው 4.4 ቢሊየን ዶላር ርዳታ የተሟላው 13 ከመቶው ብቻ ነው።

XS
SM
MD
LG