በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ350 ሺህ በላይ ዩክሬናውያን መሰደዳቸው በአውሮፓ ድምበሮች ቀውስ ፈጥሯል


የዩክሬን ስደተኞች የፖላንድን ድምበር አቋርጠው ሜዲካ ከተማ ሲገቡ
የዩክሬን ስደተኞች የፖላንድን ድምበር አቋርጠው ሜዲካ ከተማ ሲገቡ


ራሽያ በዩክሬን ላይ ያካሄደችው ወረራ እስከ 4 ሚሊየን ዩክሬናውያን ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ሊያደርግ ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህ ሳምንት አስታውቋል። ይህም በ70 አመት ታሪክ ውስጥ በአውሮፓ ያልታየ የስደተኛ ቀውስ እንደሚያስከትል ተጠቁሟል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን መረጃ እንደሚያሳየው እስካሁን 368 ሺህ ዩክሬናውያን ወደ ጎረቤት ሀገራት የተሰደዱ ሲሆን ቁጥሩ እያሻቀበ ሊሄድ ይችላል ተብሏል።

ፖላንድ፣ ሞልዶቫ፣ ሮማኒያ፣ ስሎቫኪያ እና ሀንጋሪ የራሽያን ውጊያ ሸሽተው የሚወጡ ዩክሬናውያን ስደተኞችን ለመቀበል በኮቪድ 19 ምክንያት ጥለውት የነበረውን የድምበር ላይ ቁጥጥር ያላሉ ሲሆን የፖላንድ መንግስት ድምበሩን ሙሉ ለሙሉ ክፍት በማድረግ ሰዎች ያለምንም መታወቂያ መግባት እንዲችሉ ፈቅዷል።

በተመሳሳይ የሞዶቭያን ፕሬዝዳንት ማያ ሳንዱ መንግስታቸው ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎችን ማቋቋሙን በትዊተር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል። የራሽያ ፕሬዝዳንት አጋር የሆኑት የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትርም ስደተኞች ያለምንም ማስረጃ እንዲገቡ የፈቀዱ ሲሆን በራሽያ ላይ የሚጣል ማንኛውንም ማዕቀብ እንደማትከላከል አስታውቃለች።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ምክር ቤታቸው ለዩክሬን የሚውል 6.4 ቢሊየን ዶላር እንዲያፀድቅላቸው የጠየቁ ሲሆን ከዛ ውስጥ የተወሰነው ገንዘብ ለሰብዓዊ ርዳታ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG