በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ገደብ ጣለች


ዩናይትድ ስቴትስ “በሶማሊያ ዲሞክራሲያዊ ሂደቶችን አደናቅፈዋል” በሚል በወነጀለቻቸው የዚያች አገር ባለስልጣናት እና አንዳንድ ግለሰቦች ላይ ወደ ዋሽንግተን የሚያደረጉ ጉዞዎችን የሚከለክል የቪዛ ግደባ ጥላለች።

ሶማሊያ ትላንት ሊጠናቀቅ ታቅዶ የነበረውን የአገሪቱ የፓርላማ አባላት ምርጫ ወደ መጭው መጋቢት 6, 2014 ዓም መግፋታቸውን ተከትሎ አገራቸው የቪዛ እገዳውን ውሳኔ ማሳለፏን የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን አስታውቀዋል።

"በዚህ ፖሊሲ መሰረት፣ በፈጸሙት አደናቃፊ የሆነ ምግባር ተጠያቂ ለማድረግ በበርካታ የሶማሊያ ባለስልጣናት እና ሌሎች ግለሰቦች ላይ የቪዛ እገዳ ጥለናል" ብለዋል።

ብሊንከን ይህን ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ ነው።

XS
SM
MD
LG