ዋሽንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ ሩስያ በዩክሬይን ላይ በፈጸመችው ወረራ ሳቢያ የአውሮፓ ህብረት እና ብሪታንያ የወሰዱትን ተመሳሳይ እርምጃ ተከትላ የሩስያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ሰርጌ ላቭሮቭን ንብረት እንዳይንቀሳቀስ እንደምታደርግ ይፋ አደረገች።
የዩናይትድ ስቴትስ የግምጃ ቤት ዋሽንገተን የደረሰችበትን ይህን ውሳኔ ይፋ ያደረገው የሩሲያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ንብረት እና የባንክ ሂሳቦችን እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ብራስልስ ላይ በአንድ ድምፅ መስማማታቸውን ይፋ ባደረጉበት ስብሰባ ወቅት ነው።