በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዑክሬይን እና የሩሲያ ኃይሎች ኪዬቭ ላይ ሲዋጉ ውለዋል።


UKRAINE-CRISIS/KYIV
UKRAINE-CRISIS/KYIV

የሩሲያ እና የዩክሬን ኃይሎች: አንዱ ከተማይቱን ለመቆጣጠር ሌላው ለመመከት በተፋለሙባት የዩክሬኗ ዋና ከተማ ኪየቭ: በዛሬው ዕለት የከባድ መሳሪያዎች ተኩስ እና የፍንዳታ ድምፅ ሲሰማ ውሏል። የኪየቭ ባለስልጣናት ከቀኑ አስራ አንድ ሰዓት እስከ ጧት ሁለት ሰዓት የሚቆይ የሰዓት እላፊም ደንግገዋል።

የዩክሬን ባለስልጣናት ኪየቭን ከሩሲያ ጦር ለመከላከል በያዙት ውጊያ እንዲረዷቸው ዜጎቻቸውን እየጠየቁ ነው።

በከተማይቱ የሚገኝ የጦር ሰፈር ጥቃት ቢቃጣበትም ጥቃቱን መመከቶ መመለሱን የዩክሬን ጦር አመልክቷል።

በዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጣ መሰረት አንድ ረዥም በከተማይቱ የሚገኝ የመኖሪያ አፓርታማ ህንጻ ማለዳ ላይ በሩሲያ ሚሳይል ተመቷል። አንድ የነፍስ አድን ሰራተኛ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገረው በጥቃቱ 6 ሰዎች ቆስለዋል። ጥቃቱን የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎች በሕንጻው የላይኛው ፎቆች ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን አመላክተዋል።

በኪየቭ ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት “ዛሬ ዕለት ተባብሶ ይቀጥል ይሆናል” ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ግምታቸውን ገልጠው ነበር። "ኪቭ ልዩ ትኩረት ትሻለች። ዋና ከተማችንን ልናጣ አንችልም።" ነበር ያሉት።

ዘለንስኪ በትዊተር ባሰፈሩት ጽሁፍ ላይም ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር መነጋገራቸውን ገልጠዋል።

"አጋሮቻችን የላኩት ጦር መሳሪያ ወደ ዩክሬን እየመጣ ነው። የፀረ-ጦርነቱ ጥምረት እየሰራ ነው።" ነበር ያሉት።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬኗን ደቡብ ምስራቅ ከተማ ሜሊቶፖል’ን ይዘዋል ብሏል።

የሩስያ ኃይሎች ወደ ኪየቭ እና ሌሎች ቁልፍ ከተሞች የሚያደርጉት ግስጋሴ “ጥንካሬው የታቀበ የሚመስለውን የዩክሬንን መንግስት ጨርሶ አቅም ለማሳጣት የታለመ እቅድ አካል ነው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች ምዕራባውያን ባለስልጣናት ትላንት ተናግረው ነበር።

XS
SM
MD
LG