በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የሾመቻቸው የኢምባሲው ጉዳይ ፈፃሚ አዲስ አበባ ገብተዋል


አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን
አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የነበሩትን ጊታ ፓሲን ኃላፊነት የሚረከቡትና ጉዳይ ፈፃሚ ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ዛሬ አርብ አዲስ አበባ ገብተዋል።

አምባሳደር ጃኮብሰን ከአሁኑ ኃላፊነታቸው በፊት፣ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ውጭ ጉዳይ አገልግሎት አባል ከመሆን ባሻገር በኮሶቮ፣ ታጂኪስታን፣ እና ተርኪሚኒስታን ሀገራት በአምባሳደርነት አገልግለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳይ ዋነኛ ምክትል ረዳት ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ የውጭ አገልግሎት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር እና የዋይት ኃውስ ብሄራዊ የፀጥታ ምክር ቤት ምክትል የበላይ ፀኃፊ ሆነውም አገልግለዋል።

XS
SM
MD
LG