ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ተዋሳኝ አገሮች መድረክ መገለሏ ተገቢ ያለመሆኑ ተገለጸ። የኢትዮጵያ መኖር ለቀይ ባሕር እና ለአፍሪቃ ቀንድ የኢኮኖሚ ውህደትና ሰላም አስፈላጊ መሆኑንም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተካሄደ አንድ ጥናት ጠቆመ።
በሌላ በኩል በቅርቡ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የቀረበ ህግ፣ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ መንግሥት በተመለሱ ጥያቄዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።