በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ጤና ድርጅት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ክትባት የሚያዘጋጁበት ማዕከል ሊከፍት አቅዷል


ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ድሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም
ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ድሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም የጤና ድርጅት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ክትባቶችን፣ ለካንሰር ህክምና የሚጠቅሙ መድሃኒቶችን እና ጸረ-ተዋሲያንን ለማምረት የሚያስችላቸውን ዓለም አቀፍ የሥልጠና ማዕከል እንደሚገነባ አስታውቋል።

የድርጅቱ ኃላፊ ቴድሮስ አድሃኖም አዲሱ ማዕከል የሚቋቋመው ደቡብ ኮሪያ ላይ መሆንና እና ኤምአርኤንኤ የተሰኘውን በድርጅቱ እና ደቡብ አፍሪካ ትብብር የተሰራውን ቴክኖሎጂ እንደሚያጋራ ጄኔቫ ላይ ተናግረዋል።

ይሄ ቴክኖሊጂ ተመራማሪዎች ካለ ሞዴርና ድርጅት ድጋፍ የሞዴርና ክትባትን ዳግም መስራት የቻሉበት መላ መሆኑ ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት ስድስት የአፍሪካ ሀገራት ማለትም፣ ናይጄሪያ፣ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ እና ቱኒዝያ የኮቪድ-19 ክትባቶችን የሚያዘጋጁበት የቴክኖሎጂ መመሪያ እና ዕውቀት እንደሚቀርብላቸው ይፋ አድርጓል።

XS
SM
MD
LG