በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመካከለኛው አፍሪካ በእስር የሚገኙ ሰላም አስከባሪዎችን ለማስለቀቅ ተመድ እየጣረ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ሰቴፋኒ ዱጃሪች እአአ ጁን 20/2017
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ሰቴፋኒ ዱጃሪች እአአ ጁን 20/2017

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ በሳምንቱ መጀመሪያ በቁጥጥር ስር የዋሉ 4 የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላትን ለማስለቀቅ እየጣረ እንደሆነ አስታወቀ።

አራቱ የፈረንሣይ ዜግነት ያላቸው ወታደሮች ሰኞ ዕለት ነበር በዋና ከተማዋ ባንጁል በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉት። ወታደሮቹ በወቅቱ በማዕከላዊ አፍሪካ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰላም ተልዕኮ ከፍተኛ አመራር የሆኑትን ጄኔራል ስቴፋኒ ማርቺኒዮር አጅበው እንደ ነበር ተነግሯል። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፋውስቲን አርቻንጌም በዚሁ ቀን ነበር ከቤልጂየም ወደ ሀገራቸው የሚመለሱት። ጄኔራሉ ከበረሩ በኋላ አጃቢዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይሄ ከሆነ ከግማሽ ሰዓታት በኋላ የፕሬዚዳንቱ አውሮፕላን አርፏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ሰቴፋኒ ዱጃሪች ኒው ዮርክ ላይ ለዘጋቢዎች ሲናገሩ የሰላም አስከባሪው ተልዕኮ አራቱን ግለሰቦች ለማስለቀቅ ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር ግንኙነት ተጀምሯል።

ከትናንት ጀምሮ በቁጥጥር ስር ያዋሉትን ወታደሮች በተመለከተ የሀገሪቱ ፖሊስ የሰጠው ምክንያት የለም። ይሁን እንጂ፣ ከወታደሮቹ መታወቂያ እና ታጥቀውት ከነበረው መሳሪያ ምስሎች ጋር የተሰራጩ የማህበራዊ መገናኛ መልዕክቶች፣ ፈረንሣይ ፕሬዚዳንቱን ለመግደል ማሴሯን የሚገልጹ ነበሩ።

ከሩሲያ ጋር ግንኙነት እንዳለው የተነገረ፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ዌብሳይት፣ ፈረንሣይ የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ ስትል ያወገዘቻቸውን ወንጀላዎቹን ከአተሙ አውታሮች መካከል አንዱ ነው ተብሏል።

XS
SM
MD
LG