በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የህወሓት ተዋጊዎች በአማራ ክልል የፈፀሙት ጥቃት እንደሚያሳስባት አስታወቀች


ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ
ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ

ዩናይትድ ስቴትስ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የህወሓት ተዋጊዎች በነሐሴ እና መስከረም ወር ላይ በአማራ ክልል የፈፀሙትን ፆታዊ ጥቃቶች እና ሌሎች የጭካኔ ድርጊቶችን ዘርዝሮ ያወጣው ሪፖርት እጅግ እንዳሳሰባት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ዛሬ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ቃል አቀባዩ አክለው በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች ሰብዓዊ ጥሰትን እንዲያወግዙ እና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እና እንግልት እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

"ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም በሚደረገው ጥረት ውስጥ ገለልተኛ ምርመራ ተደርጎ ለደረሱ ጥቃቶች በሙሉ ተጠያቂ እንዲኖር ጠንካራ አቋማችን ነው" ብለዋል።

ፕራይስ በመግለጫቸው በሚፈፀሙ ጥቃቶች ዙሪያ በተከታታይ የሚወጡት ሪፖርቶች እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ጦርነት በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት ያሳያል ያሉ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ከሁሉም ወገኖች ጋር በመነጋገር ጥቃቶቹንና የጭካኔ ድርጊቶቹን ለማስቆም፣ ህይወት አድን ሰብዓዊ ርዳታ ያለምንም መሰናክል ለማድረስ እና ለግጭቱ ስላማዊ መፍትሄ ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG