የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር የጀመረው ድርድር እንደሌለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ይሄም ሆኖ ግን ድርድር ሊጀመር የሚችልበት ዕድል መኖሩን ጠቁመዋል።
“ህወሓት ቀልብ ከገዛ፣ በጦርነት እንደማያዋጣውና እንደማያሸንፍ ከተገነዘበ፣ እኛ በደስታ ነው የምናየው” ብለዋል።
የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ድርድር ለማድረግ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በህወሓት የቀድሞ አመራር አባላትን ከእሥር መለቀቅ፣ የታቀደውን ሀገራዊ ምክክር፣ አሁን አፋር ውስጥ ስላለው ውጊያና ሌሎች ጉዳዮችም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሽ ያካተተውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ።