በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራን የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ ሦስት ሰዎች ገደለ


በኢራን ታብሪዝ በምትባለው ከተማ ሰሜን ምዕራብ የመኖሪያ ሰፈሮች ላይ አንድ የጦር አውሮፕላን መከስሰከሱን ተከትሎ 3 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
በኢራን ታብሪዝ በምትባለው ከተማ ሰሜን ምዕራብ የመኖሪያ ሰፈሮች ላይ አንድ የጦር አውሮፕላን መከስሰከሱን ተከትሎ 3 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

በኢራን ታብሪዝ በምትባለው ከተማ ሰሜን ምዕራብ የመኖሪያ ሰፈሮች ላይ አንድ የጦር አውሮፕላን መከስሰከሱን ተከትሎ 3 ሰዎች መሞታቸውን፣ ከሟቾቹ መካከል ሁለት የበረራ ባለሙያዎች እንደኑ የሀገሪቱ መንግሥት ቴሌቭዥን ዘገበ።

የአካባቢዊ የቀይ ጨረቃ ማህበር ኃላፊ አውሮፕላኑ ትምህርት ቤት ላይ እንደወደቀና፣ ከሟቾች መካከል አንደኛው በአካባቢው ነዋሪ የነበረ ሰው እንደሆነ ተናግረዋል።

የቀጠናው ባለሥልጣን ሞሃመድ ባጊር፣ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ትምህረት ቤቱ በወቅቱ ዝግ እንደነበረ ተናግረዋል። የተከሰከሰው አውሮፕላን ኤፍ 5 የተባለ የጦር አውሮፕላን እንደሆነ እና ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ግድም ሞናጂም በተባለው ልዩ ስፍራ እንደተከሰከሰ አስረድተዋል።

ክስተቱን በተመለከተ ምርመራ አንደቀጠለ የመንግሥቱን ቴሌቭዥን ጠቅሶ አፌፒ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG