በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሴኔጋል በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ላይ ከበድ ያለ ቅጣት እንዲጣል የሚጠይቅ ሰልፍ ተደረገ


ሰልፈኞቹ
ሰልፈኞቹ

በትናንትናው ዕለት በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን ባንዲራ በእሳት የለኮሱ ወንድ ሰልፈኞች " ሴኔጋል መቼም ቢሆን የተመሳሳይ ጾታን ግኑኝነት አትቀበልም!" በማለት መፈከር አሰምተዋል። ሌሎቹ ደግሞ ሴኔጋል የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ጉዳይ "አይሁንም!" እንዳለች፣ ይህ አጀንዳም ሊቆም እንደሚገባ የሚገልጹ መፈክሮችን ይዘው ታይተዋል።

ፐሌስ ዲ ኦብሌስክ ወደ ተሰኘው የከተማዋ ስፍራ ያቀኑት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በተመሳሳይ ጾታ ግኑኝነት ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ ከበድ ያለ ቅጣት እንዲጣል ጠይቀዋል።

ሰልፉ የተዘጋጀው በወግ አጥባቂ የእስልምና ቡድን አማካኝነት ሲሆን፣ ቡድኑ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነት በምዕራቡ ዓለም የተጫነ በሴኔጋላዊያን ባህህልና ወግ ላይ አደጋ የደቀነ መሆኑን ገልጿል።

95 በመቶ ህዝቧ የእስልምና ዕምነት ተከታይ በሆነባት ሴኔጋል፣ የሀገሪቱ ህግ "ያልተጋባ ወይንም ተፈጥሯዊ ያልሆነ" ሲል በገለጸው ግንኙነት ወስጥ የተገኙ ሰዎች እስከ 2500 ዶላር በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ደንግጓል ።

ተቃዋሚዎች ግን መንግሥት እንደዋሻቸው፣ የሚቀጣ ህግ ከነጭራሹ እንደሌለ በማንሳት ቅሬታ ያሰማሉ። ተሳታፊዎችን ከ5 እስከ 10 ዓመት በሚጠጋ እስራት ለመቅጣት የቀረበው ረቂቅ ህግ ከሰሞኑ በሀገሪቱ ህግ አውጪዎች ውድቅ ሆኗል።

XS
SM
MD
LG