በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ አዲሱ 'Truth Social' ማህበራዊ ሚዲያ ዛሬ ይለቀቃል


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የመሰረቱት 'Truth Social' የተሰኘ አዲስ የማህበራዊ ሚድያ ዛሬ በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል። ፕሬዚዳንቱም ሥልጣን ከለቀቁ ለመጀመሪያ ግዜ በአዲሱ ገፃቸው ወደ ማህበራዊ ሚዲያ እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው የምክር ቤት አባል በነበሩት ዴቪን ኖነስ የሚመራው 'ትረምፕ ሚዲያ እና ቴክኖሎጂ ግሩፕ' የተሰራው 'Truth Social' የማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ሥራ ሲጀምር፣ እራሳቸውን የመናገር ነፃነት ጠባቂ አድርገው ከሚቆጥሩት እንደ ትዊተር፣ ፌስቡክ እና ዩ ቲዩብ የመሳሰሉ ተቋማት መካከል አንዱ ይሆናል ተብሏል።

ከሳምንታት በፊት የትራምፕ የመጀመሪያ ልጅ የሆነው ዶናልድ ጁኒየር የአባቱን የትሩዝ ሶሻል ገፅ የሚያሳይ ምስል "ተዘጋጁ፣ የምትወዱት ፕሬዚዳንታችሁ በቅርቡ ያያችኃል" ከሚል ፅሁፍ ጋር በትዊተር ገፁ አጋርቶ ነበር።

XS
SM
MD
LG