በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክር ቤቱ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በኮሚሽነርነት የሚያገለግሉ ዕጩዎችን አጸደቀ


(ፎቶ፡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌስቡክ ገፅ ላይ የተወሰደ)
(ፎቶ፡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌስቡክ ገፅ ላይ የተወሰደ)

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ እና አካታች ምክክር እንዲያካሄድ በአዋጅ ለተቋቋመው ኮሚሽን በኮሚሽነርነት የሚያገለግሉ 11 ግለሰቦችን ሹመት ዛሬ አጸደቀ።

ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙ ሲሆን ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል።

አስራ አንዱ ተመራጮች ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በኮሚሽነርነት እንዲያገለግሉ ለዕጩነት ከተጠቆሙ 632 ግለሰቦች መካከል የተመረጡ ሲሆን ምክር ቤቱ ሹመታቸውን ያፀደቀው በአምስት ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ ነው።

የአመራረጡትን ሂደት አስመልክተው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ የሰጡት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ በምርጫ ሂደቱ ውስጥ የኃይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች በሂደቱ ተሳታፊ እንደነበሩ አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG