በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካናዳ ፖሊሶች የኮቪድ ክልከላ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ተሰማሩ


የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ ክልከላዎችን በመቃወም የኦታዋ ከተማን እምብርት በመቆጣጠር ሰፍረው የነበሩ የከባድ መኪና ሾፌሮች እና ተቃውሞ ሰልፈኞችን ለመበተን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የካቲ 18/2022 ዓ.ም ወደ ስፍራው ያቀናው ፖሊስ።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ ክልከላዎችን በመቃወም የኦታዋ ከተማን እምብርት በመቆጣጠር ሰፍረው የነበሩ የከባድ መኪና ሾፌሮች እና ተቃውሞ ሰልፈኞችን ለመበተን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የካቲ 18/2022 ዓ.ም ወደ ስፍራው ያቀናው ፖሊስ።

ከሦስት ሳምንት በላይ ለሆነ ጊዜ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ ክልከላዎችን በመቃወም የኦታዋ ከተማን እምብርት በመቆጣጠር ሰፍረው የነበሩ የከባድ መኪና ሾፌሮች እና ተቃውሞ ሰልፈኞችን በመበተን ከተማዋን ወደ ነበረችበት ለመመለስ ያቀደው የካናዳ ፖሊስ ትላንት ወደ ሥፍራው ተንቀሳቀሷል ።

በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖሊስ ኃይል አባላት ፣ (አንዳንዶቹም ፈረሰኛ ፖሊሶች ናቸው) አርብ ዓመሻሹን በጀመሩት ዘመቻ አራት አስተባባሪዎችን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰልፈኞች በቁጥጥር ስር አውለዋል። ፖሊሶቹ ሰልፈኞችን በቀስታ ከባድ መኪኖች ከቆሙበት ስፍራ እያገፉ ሲያስወጧቸው ተይቷል ።

ከትላንት በስቲያ የነበረው ዘመቻ ትንቅንቅ የነበረበት እንደሆነ ተጠቁሟል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች ከመኪናቸው እየተጎተቱ እንዲወጡ ተደርጓል፣ፖሊስ እርምጃውን ለመገዳደር የሞከሩትን መሬት ላይ እየጣለ ፣ በፕላስቲክ ካቴና የፊጥኝ ሲያስርም ታይቷል።

"ጥያቄዎቻችን ረብ የለሽ አይደሉም፣ የኮቪድ እግዶች እንዲነሱ እንሻለን” ብሏል ። ጎርድ የተሰኘ በድንበር ተሻገሪው የክትባት ግዳጅ ምክንያት ለመስራት እንደተሳነው የገለጸ የጭነት መኪና ሾፌር

ፖሊስ ትናንት 21 ዛሬ ደግሞ ከደርዘን ያላነሱ የጭነት መኪኖችን የተቃወሚ መኪኖችን ከስፍራዎቹ እነዳስነሳ ሮይተርስ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG