በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱኒዚያን ፕሬዝደንት በማንቋሸሽ የተከሰሱ የፓርላማ አባል የእስር ቅጣት ተላለፈባቸው


ፋይል- የቱኒዚያ ፕሬዚደንት ካይስ ሳይድ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 20/2021 ዓ.ም ሲዳኢ ቦውዚድ ውስጥ ንግግር ሲያደርጉ
ፋይል- የቱኒዚያ ፕሬዚደንት ካይስ ሳይድ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 20/2021 ዓ.ም ሲዳኢ ቦውዚድ ውስጥ ንግግር ሲያደርጉ

የተበተነው የቱኒዚያ ፓርላማ አባል የሆኑት ያሲን አያሪ ፕሬዝዳንቱን የሚያንቋሽሽ ንግግር አድርገዋል በሊል በቀረባበቸው ክስ ጦር ፍርድ ቤቱ በሌሉበት የእስር ቅጣት እንደ ወሰነባቸው ለሮይተርስ ተናገሩ ።


ፕሬዚደንቱ የሀገሪቱን ፓርላማ ሥልጣን አልባ የሚያደርግ ውሳኔ መወሰናቸውን የተቃወሙት ያሲን አያሪ “የጦር መፈንቅለ መንግሥት” በማለታቸው ፕሬዚደንቱን እና የጦር ሰራዊቱን ሰድበዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የዐስር ወር እስር ተፈርዶባቸዋል።

ፕሬዚደንት ካይስ ሳይድ ፣ በአውሮፓዊያኑ ሐምሌ 25 ፓርላማውን ከበተኑ በኋላ ፣ የመንግሥት መዋቅር ሥልጣንን ውድቅ በማድረግ የአብዛኞቹን መስሪያቤቶች ኃላፊነቶች መቆጣጠራቸው ሰፊ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ውግዘት አምጥቶባቸዋል።
የሀገሪቱን ጠቅላይ ፍርድ ምክር ቤት በተመሳሳይ ያገዱት ፕሬዚደንት የአሁኑ የእስር ውሳኔ ፣ ተቀናቃኞቻቸውን ሊበቀሉ ይችላሉ የሚለውን የተቃዋሚዎቻቸው የቀደመ ስጋት አጠናክሯል።


በአሁኑ ጊዜ በፓሪስ የሚገኙት ያሲን አያሪ የተፈረደባቸውን እስራት በተመለከተ ለሮይተርስ በስልክ ሲናገሩ ፣ “ ትናንት በብራሰልስ ሳኢድ ፣ አምባገነን እንዳልሆኑ ተናገሩ።

ዛሬ ግን የጦር ፍርድ ቤቱ በአንድ ሕግ አውጪ ላይ፣ የመናገር መብትን በተጻረረ መልኩ የእስር ቅጣት ፈረደበት’’ ሲሉ ፕዝደንቱን ወቅሰዋል። ፕሬዝደንቱ በአውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር 2011 ዓ.ም በሀገሪቱ የፈነዳው አብዮት ውጤት የሆኑ መብቶች እና ነጻነቶችን እንደሚያስከብሩ፣ ዴሞክራሲን ወደ ቱኒዚያ እንደሚያመጡ ፣ ከወራት በኃላ ሕዝበ ውሳኔ እንደሚከናወንና አዲስ ሕገ መንግሥትም እንደሚረቀቅ ተናግረዋል። በዓመቱ መጨረሻ አዲስ ፓርላማ ምርጫ እንሚደረግም አክለዋል ።

XS
SM
MD
LG