በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በትንሹ 13 ሰዎች ተገደሉ


ፋይል- የሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች በሶማሊያ መቋድሾ በሚገኘው የፕሬዝዳንዱ ቤተ መንግስት አቅራቢያ ወደ ፍተሻ የሚወስደን መገድ ሲጠብቁና ፍተሻ ሲያደረጉ በሚገኝ ፍተሻ ላይ ወደ ፍንዳታው ቦታ የሚወስደውን መንገድ ጠብቀዋል። /የካቲት 3/2014
ፋይል- የሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች በሶማሊያ መቋድሾ በሚገኘው የፕሬዝዳንዱ ቤተ መንግስት አቅራቢያ ወደ ፍተሻ የሚወስደን መገድ ሲጠብቁና ፍተሻ ሲያደረጉ በሚገኝ ፍተሻ ላይ ወደ ፍንዳታው ቦታ የሚወስደውን መንገድ ጠብቀዋል። /የካቲት 3/2014

ትላንት በማዕከላዊ ሶማሊያ በምትገኘው በልደዋኒ ከተማ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ቦንብ ጥቃት 13 ሰዎች መሞታቸውን የመንግስቱን ቴሌቭዥን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል ።

ጥቃቱ የደረሰው የአካባቢው ባለስልጣናት እና ፖለቲካ ሰዎች ተጨናንቆ በነበረ ሬስቶራንት ላይ እንደነበረ የዐይን ምስክሮች ተናግረዋል ። ሳይት የተባለው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድንን የበይነ መረብ እንቅስቃሴ የሚከታተል ስብስብ ፣ ቡድኑ ለጥቃቱ ኃላፊነት እንደወሰደ ጠቁሟል።

ጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ሁለት ጥቃቶችን ፈጽሟል። በጥቃቱ ተጨማሪ 18 ሰዎች መቁሰላቸውን የሶማሊያ መንግሥት በቲዊተር ገጹ ላይ አስታውቋል ።

የቆሰሉ ሰዎችን ለመርዳት እንደጣሩ የተናገሩ አንድ የዐይን እማኝ ፣ ወታደሮች እና ሲቪሎችን ጨምሮ ሰባት አስክሬኖችን መቆጠራቸውን እና ከ10 በላይ መቁሰላቸውን ለሮይተርስ ተናግረዋል ።

ፖሊስ እና የመንግሥት ባለሥልጣን ጥቃቱ የተፈመው በአጥፍቶ ጠፊ አማካይነት መሆኑን ቢያረጋግጡም፣ የተጎጂዎችን ቁጥር ግን ይፋ አላደረጉም ። ምርጫን በተመለከተ ሰሞነኛ ውዝግብ የተነሳባት ሶማሊያ በአልሸባብ የቅርብ ጊዜ ጥቃቶች ምክንያት ቀን ያልተቆረጠለት የሀገሪቱ ፓርላማዊ ምርጫ ሁኔታ ተጨማሪ ችግር እንዳይገጥመው ተሰግቷል ።

አልሸባብ የሀገሪቱን መዕከላዊ መንግሥት በመገርሰስ በእስላማዊ ህግጋት የሚመራ አስተዳደር በሀገሪቱ የመተካት ዓላማ እንዳለው ሮይተርስ አስታውሷል።

XS
SM
MD
LG