በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሲፒጄ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እንደ አዲስ ለመክሰስ እና ለመመርመር መወሰኗን ተቃወመ


ከግራ ወደ ቀኝ ለአሶሼትድ ፕረስ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል አሚር አማን ኪያሮ ሲሆን ቀጥሎ ያለው ደግሞ ተራራ ኔትወርክ የተሰኘው የበይነ መረብ ባለቤት ታምራት ነገራ። ( ፎቶ - ለሲፒጄ - ሲሳይ ታከለ ተራራር ኔትወርክ)
ከግራ ወደ ቀኝ ለአሶሼትድ ፕረስ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል አሚር አማን ኪያሮ ሲሆን ቀጥሎ ያለው ደግሞ ተራራ ኔትወርክ የተሰኘው የበይነ መረብ ባለቤት ታምራት ነገራ። ( ፎቶ - ለሲፒጄ - ሲሳይ ታከለ ተራራር ኔትወርክ)

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት በሁለት ጋዜጠኞች ላይ የከፈቱትን ክስና በአንድ አርታኢ ላይ የተጀመረን አዲስ ምርመራ እንዲያቋርጡ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋም ሲፒጂ አሳሰበ። ሀገሪቱ ጋዜጠኞችን ለመቅጣት በማሰብ የምታካሄዳቸውን እስሮች መግታት እንዳለባትም ትላንት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል ።

ለአሶሼትድ ፕረስ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል አሚር አማን ኪያሮ ፣ ለተለያዩ የዜና አገልግሎቶች በካሜራ ባለሞያነት የሚሠራው ቶማስ እንግዳ ፣ እንዲሁም ተራራ ኔትወርክ የተሰኘው የበይነ መረብ ባለቤት ታምራት ነገራ ኢትዮጵያ የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባወጀች ማግስት ከታሰሩ ጋዜጠኞች መካከል እንደሚገኙበት ሲፒጄ በመግለጫው አስታውቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱን ተከትሎም ጋዜጠኞችን ጨምሮ በአዋጁ ሰበብ የተያዙ ሁሉም ሲቪሎች በሕጉ መሰረት በ48 ሰዓታት ውስጥ ይፈታሉ የሚል ግምት እንደነበረርውም ጠቁሟል።

ይሁንና አዋጁ መነሳቱ በተነገረ በሁለተኛው ቀን ማለትም የካቲት 10 /2014 የአሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ታምራት ነገራ ላይ አዲስ ምርመራ መጀመሩን ፣በአሚር እና ቶማስ ላይ በሀገሪቱ የጸረ-ሽብር ህገ መሰረት መደበኛ ክስ እንደሚቀርብባቸው ስለመነገሩ ከቤተሰቦቻቸው እንደሰማ ሲፒጄ አስታውቋል ።

በእነዚህ ጋዜጠኞች ላይ የተጀመረው አዲስ የሕግ ሂደት እና ምርመራ ፣ ጋዜጠኞችን በእስር ለማቆየት በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በግልጽ የተወጠነ የሚረብሽ ዘዴ መሆኑን የተናገሩት የድርጅቱ ከሰሃራ በታች ተወካይ ሙዞኪ ሙሞ ፣ ባለስልጣናት አሚር አማን ኪያሮ እና ቶማስ አንግዳን በሽብር ወንጀል የመክሰስ ሂደትን እንዲሁም ፣ በታምራት ነገራ ላይ ይደረጋል የተባለውንም ምርመራ እንዲያቋርጡ አሳስበዋል ።

ሲፒጄ የአሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ ኃይሉ አዱኛ እና የክልሉን የፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርደሳ ለተደረገላቸው የስልክ ጥሪም ሆነ የስልክ ጽሑፍ መልዕክት መልስ አለመስጠታቸውን ጠቅሷል ።

XS
SM
MD
LG