በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ለመፍታት የተጀመረው እንቅስቃሴ “ተስፋ ሰጭ ነው” ሲሉ ትግራይ ክልልን በማስተዳደር ላይ የሚገኙት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ህወሓት የተመሠረተበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።
ይሁን እንጂ “እንቅስቃሴው እንቅፋት ገጥሞታል” ሲሉም አክለዋል።
“የማንደራደርባቸው” ሲሉ የገለጿቸው ነጥቦችንም ዘርዝረዋል።