በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት ለአምነስቲ ሪፖርት ምላሽ ሰጠ


“የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል በቆቦና በጭና የፈፀሙት ጥቃት የጦር ወንጀልና በሰብዕና ላይ የተፈፀመ ወንጀል ሊሆን ይችላል” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከትናንት በስተያ ረቡዕ ላወጣው ሪፖርት ህወሓት ዛሬ በሰጠው ምላሽ “የትግራይ መንግሥትና የትግራይ ሠራዊት በሲቪሎች ላይ ያተኮረ ጥቃትን አይደግፉም” ብሏል።

አክሎም “በሠራዊታችን ጉዳት ለደረሰባቸው ተጠቂዎች ልባችን ይሰበራል፤ ይህንን የፈፀሙ የሠራዊታችን አባላትን የትግራይ መንግሥት ምርመራ አድርጎ ለፍትህ ያቀርባቸዋል” ብሏል።

የህወሓት መግለጫ በመቀጠል “የአብይ መንግሥትና የአማራ መሪዎች ሲቪሎች ያለምንም መሣሪያ በጦርነት ላይ እንዲሳተፉ ሲያደርጉ በነበሩት ቅስቀሳ ምክንያት ለዚህ ተዳርገዋል” ይልና “በአንፃሩ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በዚህ ሪፖርት ላይ መሠረታዊ መረጃዎችን ባለማካተት የትግራይ ኃይሎችን በጦር ወንጀል ለመክሰስ ቸኩሏል” ሲል ወቅሷል።

ክሦቹ በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠይቋል።

ህወሓት ለአምነስቲ ሪፖርት ምላሽ ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00

XS
SM
MD
LG