በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጉቴሬሽ ቃል አቀባይ ስለ ኢትዮጵያ


ስቴፋን ዱያሪች
ስቴፋን ዱያሪች

በአፋር ሰሜናዊ አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ የሰብአዊ ሁኔታው መበላሸት መባባሱንና የረድዔት አጋሮቻቸው ተፈናቃዮችን መድረስ አለመቻላቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬሽ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱያሪች ትናንት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

መድረስ በሚቻልባቸው ሰባት ወረዳዎች ውስጥ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ 80 ሺህ የሚሆኑ ህፃናት፣ ለነፍሰ ጡሮችና አጥቢ እናቶች ዕርዳታ እየተከፋፈለ መሆኑን ገልፀዋል።

ተንቀሳቃሽ የጤና አገልግሎትና የምግብ አቅርቦት ቡድኖቻቸው በ14 ወረዳዎች ለተረጂዎች ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን አመልክተው ወደ መቀሌም የህክምና ቁሳቁስ ባለፈው ሣምንት በአይሮፕላን መላካቸውን አስታውቀዋል።

ባለፈው ዓርብም የዓለም ጤና ድርጅት የህክምና መገልገያ መሣሪያዎችን፣ ፀረ ተሃዋስያን፣ የወባና የስኳር እንዲሁም ለሥነ ተዋልዶ ጤና የሚውሉ መድሃኒቶችን ጨምሮ 10 ሜትሪክ ቶን የሚደርስ የህክምና ቁሳቁስ መጓጓዙንም ዱያሪች ተናግረዋል።

ትግራይ ውስጥ የነዳጅ እጥረት እንዳለ የጠቆሙት ዱያሪች የነዳጅ ቦቴዎችና የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ዚያ እንደማይገቡ፣ ይህ ደግሞ እርዳታ በስፋት የማከፋፈል አቅምን እንደሚገድብ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG