በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ድጋፍ እየደረሰ ነው


በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ በአፋርና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ለተጎዱ ወደ 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ በአፋርና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ለተጎዱ ወደ 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ በአፋርና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ለተጎዱ ወደ 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጋቸውን ፌደራል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

“አይዞን ኢትዮጵያ” የተባለ መተግበሪያን በመጠቀም የተሰበሰበው ገንዘብ በቀጥታ ወደ ኮሚሽኑ የገባ ሲሆን በዚሁ ገንዘብ የተገዛው የመጀመሪያ ዙር እርዳታም ወደ አፋርና ወደ አማራ ክልሎች መደረሱ ተገልጿል።

መተግበሪያውን ያዘጋጁ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ከነፍስ አድን ድጋፍ ባሻገር መልሶ በማቋቋም ጥረት ውስጥም ሰፊና የጎላ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚፈልጉ፣ ለዚህም የመተገሪያውን ተደራሽነት እንደሚያሳድጉ በተወካያቸው አማካኝነት ገልፀዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ድጋፍ እየደረሰ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:45 0:00

XS
SM
MD
LG