“ትግራይና እኛ አንድ አገር እንጂ ሁለት አገር መሆናችንን አናውቅም” ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኡለማ ምክር ቤት አባልና የሰላምና ሕግ ዘርፍ ኃላፊ ሼህ መሐመድ ሲራጅ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የራሱን ምክር ቤት ማቋቋሙን በተመለከተ ላሳለፈው ውሳኔ ምላሽ ሰጥተዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሱልጣን ሃጂ አማን የግላቸው መሆኑን ገልፀው በሰጡት አስተያየት “አሁን በጦርነቱ ምክኒያት መገናኘት አልተቻለም፤ ጦርነቱ ቆሞ ሰላም ሰፍኖ መገናኘት ሲቻል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማስተካከል ኃላፊነት አለበት። እስከዚያ እኔ በግሌ ሕጋዊ ናቸው ብዬ አላምንም” ብለዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።