በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በብራስልስ ጉባኤ ተገኙ


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአፍሪካ ኅብረትና በአውሮፓ ኅብረት የጋራ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ዛሬ ብራስልስ ናቸው።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአፍሪካ ኅብረትና በአውሮፓ ኅብረት የጋራ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ዛሬ ብራስልስ ናቸው።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአፍሪካ ኅብረትና በአውሮፓ ኅብረት የጋራ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ዛሬ ብራስልስ ገቡ።

የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከተነሳ ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ምዕራብ አውሮፓ ባደረጉት በዚህ የመጀመሪያ ጉዟቸው ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚቸል ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ፅህፈት ቤታቸው በማኅበራዊ ገፁ ላይ አስታውቋል።

“ከአፍሪካ ኅብረት እና ከአውሮፓ ኅብረት የጋራ ጉባዔ አስቀድሞ ከወዳጄ ፕሬዚደንት ቻርልስ ሚሼል ጋር ተገናኝተናል። የአውሮፓ ኅብረት እና የኢትዮጵያን ግንኙነት፣ ቀጣናዊ እንዲሁም አህጉራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ውጤታማ ውይይት አድርገናል” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊትር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

XS
SM
MD
LG