በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞቃዲሾው የአል-ሸባብ ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ


የአል ሸባብ ታጣቂዎች ሶማሊያ ሞቃዲሾ ውስጥ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ያደረሰው ጥቃት
የአል ሸባብ ታጣቂዎች ሶማሊያ ሞቃዲሾ ውስጥ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ያደረሰው ጥቃት

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ የአል-ሸባብ ታጣቂዎች ዛሬ ማለዳ ላይ በበርካታ የፖሊስ ጣቢያዎች እና የጸጥታ ኬላዎች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት እስካሁን አምስት ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ፤ ታጣቂዎቹም ይህንኑ አረጋግጠዋል።

የሶማሊያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል አብዲፈታህ አደን ሀሰን እንደተናገሩት ከለሊቱ 7 ሰዓት ጥቂት ቀደም ብሎ የጀመረው የአልሻባብ ጥቃት በፖሊስ ጣቢያዎች እና ካህዳ እና ዳሩሳላም የተባሉ በአመዛኙ ጸጥታ በሰፈነባቸው ከከተማይቱ ወጣ ብለው በሚገኙ ሁለት መንደሮች ላይ የተነጣጠረ ነው።

የሶማሌ ብሄራዊ ቲሌቭዥን ጣቢያ እንደዘገበው በጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ ሁለት ህጻናት ይገኙባቸዋል። ሌሎች በጥቃቱ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው በርካታ ሰዎችም ለሕክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታሎች መምጣታቸውን የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG