በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳት በድርቅ ማለቃቸው ተገለፀ


በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ እንደሚጋለጡ የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስጠንቅቋል
በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ እንደሚጋለጡ የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስጠንቅቋል

በአፍሪካ ቀንድ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳትን በድርቅ ሳቢያ ማለቃቸው ተዘገበ።

አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ እና የእርሻ ፕሮግራም ከፍተኛ ባለሥልጣን እንዳመለከቱት በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው ድርቅ እስካሁን ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳትን ሲገድል እና የሰብል ምርት በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጓል።

ባለፈው አርብ ወደ ክልሉ ተጉዘው የተመለሱት ያለም ምግብ ፕሮግራም የአደጋ ጊዜ እና ተቋቋሚነት ዳይሬክተር ሬይን ፖልሰን አስቸኳይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያቻልበት "በጣም ጠባብ መስኮት" ነች ያለችው። ሁለቱ ወሳኝ ነገሮች የፊታችን መጋቢት እና ግንቦት ወራት መሃከልበአካባቢው ረጅም የዝናም ጊዜ ተስፋ እንደሚጣልበት የቱን ያህል ጠቀም ያለ ዝናም ይጥላል? እና ድርጅቱስ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የሚፈልገውን የ130 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ያገኛል የሚሉት ናቸው።” ብለዋል።

እንደ ድርጅቱም ግምት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1981 ወዲህ ታይቶ የማያውቅ አካባቢውን የመታው ድርቅ በአፍሪካ ቀንድ 13 ሚልዮን ሕዝብ ለረሃብ አጋልጧል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከዚህ ውስጥ አስቸኳይ ዕርዳታ ለሚያስፈልገው ቁጥሩ 4 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ለሚደርስ ህዝብ ለመጪው ስድስትር ወር የ$327 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገዋል።

XS
SM
MD
LG