በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ውስጥ የረሃብ ቸነፈር አስግቷል


በድርቅ ከተጠቁ አካባቢዎች የተሰደዱ ሶማሊያውያን በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ጊዜያዊ ካምፕ ሲደርሱ እአአ ፌብሩዋሪ 4/2022
በድርቅ ከተጠቁ አካባቢዎች የተሰደዱ ሶማሊያውያን በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ጊዜያዊ ካምፕ ሲደርሱ እአአ ፌብሩዋሪ 4/2022

ለዓመታት የዘለቁ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ አደጋዎች በሶማሊያ ሰብሎችን በማውደም፣ የውሃ ምንጮችን በማድረቅ፤ ገዳይ በሽታዎች የሚዛመቱበት አመቺ ሁኔታ መፈጠርን ጨምሮ ቸነፈር ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ ተቃርቧል ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት አስጠነቀቀ።

ዩኒሴፍ አክሎም ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይህም ከአጠቃላይ ህዝቡ አንድ አራተኛው ማለት ነው፤ የሰብአዊ እርዳታ ያስፈልገዋል።

ቁጥራቸው 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚደርሱ ህጻናት ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተዳረጉ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 330 ሺ ያህሉ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እና የሰውነት መሟሸሽ ከመጋለጣቸውም በላይ ልዩ ህክምና ካላገኙ ለህልፈት ሊዳረጉ ይችላሉ” ብሏል።

በሶማሊያ የድርጅቱ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ቪክቶር ቺኒያማ እንዳስረዱት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአፋጣኝ የንጹህ ውሃ አቅርቦት ይሻሉ።የውሃ እጥረት እንደ ኩፍኝ፣ ኮሌራ እና ተቅማጥን ለመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎችን በመቀስቀሱ ወደ ከባድ ወረርሽኝ እያመራ ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልጠዋል።

በተጨማሪም በችግር ሳቢያ ተፈናቅለው ከቦታ ወደ ብኦታ ለመንቀሳቀስ የተገደዱ ሕጻናት ለሌሎች መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰቶችም ይጋለጣሉ ብለዋል።

"እንደ ጾታዊ ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ይጠብቋቸዋል። ሶማሊያ ውስጥ ባለው ሁኔታ የህጻናትን የመታገት እጣ፣ ለምሳሌም ያህል እንደ አል ሸባብ ባሉ የታጠቁ ኃይሎች የመመልመል ፈተና ሳናነሳ ስለ መፈናቀል ልናወራ አንችልም።"

ዩኒሴፍ ባለፈው አመት ባወጣው ሪፖርት እንደጠቆመው ሴት ልጆችን ጨምሮ 1,200 ህጻናት በታጣቂ ቡድኖች ሲመለመሉ፤ ሌሎች 1,000 ህጻናት ደግሞ ታፍነው ተወስደዋል። ቺኒያማ እንደሚሉት ከእነዚህ ልጆች ውስጥ አብዛኞቹ ለድርብርብ መብት ጥሰቶች ሰለባ ሆነዋል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG