በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ትግራይ ውስጥ ነዳጅ ተቸገርኩ'' የዓለም የጤና ድርጅት


መቀሌ
መቀሌ

የዓለም ጤና ድርጅት እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ካለፈው የሃምሌ ወር 2021 ዓም አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን ትግራይ ማድረስ ቢችልም፤ በክልሉ ለሚገኙ የጤና ጣቢያዎች ለማከፋፈል ግን ለሚጠቀምባቸው ተሽከርካሪያዎች የሚያውለው ነዳጅ ያለመኖሩን አመለከተ።

ያለሙ ጤና ድርጅት አክሎም ወደ ክልሉ የገባው አስፈላጊ የሆኑ የሕክምና ቁሳቁስ መከፋፈል እስከሚችልበት ጊዜ ድረስ መጋዘን ውስጥ መቀመጡን ገልጦ ከሕክምና አቅርቦቶቹም ውስጥ የሕክምና መሣሪያዎች፣ የግል ንጽሕና መጠበቂያዎች፣ የፀረ-ተዋስያን መድኃኒቶች፣ የወባና የስኳር በሽታ መድሃኒቶችን፣ ከባድ የምግብ እጥረት የሚያስከትላቸው ጉዳቶች ማከሚያ እና እንዲሁም የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት መድኃኒቶች እንደሚገኙበት አስታውቋል።

“አጋራችን” የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ደብሊውኤፍፒም ከያዝነው ወር መጀመሪያ አንስቶ የምግብ አቅርቦቶቹን በአውሮፕላን ወደ መቀሌ ማጓጓዝ ጀምሯል” ያለው የዓለም ጤና ድርጅት በያዝነው ሳምንትም ተጨማሪ ጭነት ለማጓጓዝ መታቀዱን አመልክቷል።

በህዳር ወር በድብሊውኤፍፒ ሁለት የነዳጅ ጫኚ ተሽከርካሪዎች አማካኝነት ከተጓጓዘው በስተቀር ካለፈው የነሃሴ ወር አንስቶ ነዳጅ ወደ ትግራይ እንዲገባ ባለመፈቀዱ የነዳጅ፣ የጥሬ ገንዘብ እናሌሎች አቅርቦቶች እጥረት በትግራይ የሚካሄደው የሰብአዊ አቅርቦት አገልግሎት እንዲቀንስ ወይም እንዲቋረጥ አድርጓል።” ብሏል።

በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር በህጻናት፣ ነፍሰ ጡር እና ጡት በሚያጠቡ እናቶች የገጠማቸው የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አሁንም በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን ጠቅሶ፣ ለምሳሌ በቅርብ ወራት ውስጥ በተደረጉ የስነ-ምግብ ማጣሪያ ጥናቶች 71 በመቶው ነፍሰ ጡር እና ጡት የሚያጠቡ እናቶች ትግራይ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳለባቸው አመልክቷል” ብሏል። ይህ አሃዝ በአፋር ክልል 45 ከመቶ በአማራ ደግሞ 14 ከመቶ ነው ያለው።

በአንፃራዊነት ሲታይ አዳጋችነቱ የተሻለ በሆነባቸው የአማራ እና የአፋር ክልሎች መጠኑ 84 ሜትሪክ ቶን የሚደርስ የሕክምና አቅርቦቶችን ባለፈው የታህሳስ ወር ማድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ትግራይ-አፋር ድንበር ላይ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ተረጂዎች ከ15 እሰከ 20 ሜትሪክ ቶን የሚደርስ ተጨማ የሕክምና አቅርቦቶችን የማድረስ ውትን እንዳለው አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG