በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዘጠኙ ድርጅቶች ጥምረትና የሁለት ወገን አስተያየት (ክፍል ሁለት)


አቶ ውብሸት ሙላት የሕግ ምሑር፣ አቶ ዩሃንስ አብርሃ የቀድሞ ዲፕሎማት ሲሆኑ አሁን ካናዳ ይገኛሉ
አቶ ውብሸት ሙላት የሕግ ምሑር፣ አቶ ዩሃንስ አብርሃ የቀድሞ ዲፕሎማት ሲሆኑ አሁን ካናዳ ይገኛሉ

ከሁለት ሳምንት በፊት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ መግለጫ የሰጡ የፖለቲካ ድርጅቶች ህወሃትና ኦነግን ጨምሮ ዘጠኝ ሆነው የኢትዮጵያ ፌደራሊስትና ኮንፌደራሊስት ኃይሎች ጥምረት በሚል መመስረታቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ጥምረቱ በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በኃይል በማውረድ የሽግግር ሂደት እንዲኖር ለማድረግ እንደሚሠራም ይፋ አድርገዋል።

በዚህ ጉዳይ ሁለት እንግዶችን አነጋግረን ዘገባ አሰናድተናል። አቶ ዩሃንስ አብርሃ የቀድሞ ዲፕሎማት ሲሆኑ አሁን ካናዳ ይገኛሉ። የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን በመወከል በውጭ አገር እንቅስቃሴ የሚያደርግ ኮሚቴ ጋር አብረው በመሥራት ላይ ይገኛሉ። የጥምረቱ አስተባባሪ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

አቶ ውብሸት ሙላት የሕግ ምሑር ናቸው። በተለያዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ አስተያየት በመስጠት ይታወቃሉ።

በጥምረቱና ተያያዠ በሆኑ ጉዳዮች የሁለቱን አስተያየት ጠይቀን ቅዳሜ ምሽት ክፍል አንዱን የውይይት ክፍል አስደምጠናችሁ ነበር። ክፍል ሁለቱ ይቀጥላል።

የዘጠኙ ድርጅቶች ጥምረትና የሁለት ወገን አስተያየት (ክፍል ሁለት)
please wait

No media source currently available

0:00 0:23:14 0:00

XS
SM
MD
LG