በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዞለንስኪ በሃገራቸው እና በሩሲያ የጦርነት ጉዳይ የጀርመኑን መራሄ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ፣ የጀርመኑን ቻንስለር ኦላፍ ሾልስን በኪየቩ እአአ ፌብሩዋሪ 14/2022
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ፣ የጀርመኑን ቻንስለር ኦላፍ ሾልስን በኪየቩ እአአ ፌብሩዋሪ 14/2022

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ምዕራባውያን መሪዎች የሩሲያ ወረራ ባሳደረው ሥጋት ለዩክሬይን አጋርነታቸውን እየገለጹ ባሉበት ባሁኑ ወቅት፤ የጀርመኑን መራሄ መንግሥት ቻንስለር ኦላፍ ሾልስን ዛሬ ሰኞ ኪየቭ ውስጥ ተቀብለው አነጋገሩ።

ነገ ማክሰኞ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመገናኘት ወደ ሞስኮ የሚያቀኑት ሾልስ፡ ሩሲያ እየናረ የመጣውን የጦርነት ሥጋት ደቃኝ ምልክቶች መቀነስ እንድታሳይ ጥሪ አቅርበዋል።

“ተጨማሪ ወታደራዊ ጥቃት አስከፊ መዘዝ ያስከትላል” ሲሉም በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የሩስያ ድርጊት ለአውሮፓ ሰላም በጣም አሳሳቢ አደጋ መደቀኑንም ተናረዋል።

ሩሲያ ዩክሬንን ብትወር የሚሰጡትን ተለየ ምላሽ አስመልክቶ እስካሁን በይፋ ባይናገሩም፤ ምዕራባውያን መንግሥታት እንደሚወስዱት ደጋግመው ከገለጹት አንድ ምላሽ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ የምጣኔ ሃብት ማዕቀብ መጣል እንደሚሆን አመልክተዋል።

የG-7 የገንዘብ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ “ከሁሉ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ሁኔታውን ለማርገብ የሚደረገውን ጥረት መደገፍ ነው። ሆኖም በተለይ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገው ማንኛውም ተጨማሪ ወታደራዊ ጥቃት ፈጣን፣ የተቀናጀ እና ጠንካራ ምላሽ እንደምንሰጥ ደግመን እንገልፃለን። በሩሲያ ምጣኔ ሃብት ላይ ግዙፍ መዘዝ የሚያስከትል የምጣኔ ሃብት እና የፋይናንስ ማዕቀብ በጋራ ለመጣል ተዘጋጅተናል።" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG