በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤልጂየም ለኮቪድ-19 የጤና ህግጋትን ተቃዋሚ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ሰልፈኞች እየተዘጋጀች ነው


የቤልጂየም ፖሊሶች ከአውሮፓ ህብረት ተቋማት ህንፃዎች አካባቢ ጥበቃ እያደረጉ፤ እአአ ፌብሩዋሪ 22/2022
የቤልጂየም ፖሊሶች ከአውሮፓ ህብረት ተቋማት ህንፃዎች አካባቢ ጥበቃ እያደረጉ፤ እአአ ፌብሩዋሪ 22/2022

ቤልጂየም በዛሬው ዕለት የኮቪድ-19 የጤና ህግጋትን በመቃወም በከባድ መኪና አሽከርካሪዎች “የነፃነት ኮንቮይ” የሚል ስያሜ የሰጡት ሰልፍ ወደ ዋና ከተማዋ ብራስልስ ማቅናቱን ቀጥሏል።

ሆኖም ባለሥልጣናቱ በብራስልስ በተሽከርካሪዎች የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎችን አግደዋል። በተለያዩ የቤልጂየም ድንበሮች ላይም የፍተሻ ኬላዎችን አቁመዋል።

የቤልጂየም ጠቅላይ ሚንስትር አሌክሳንደር ደ ክሩ በአንዳንዶች ተቃውሞ የቀረበባቸውን ክልከላዎች አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፡"ቀድሞውንም በጣም ከባድ የሚሰኙ የቁጥጥር ህጎች አልነበሩንም። አሁንም ተፈጻሚን የምናደጋቸው አዳዲስ ህጎች የሉም። ስለሆነም ቅሬታ ማሰማት የመረጠ ከመኖሪያ ቤቱ ሆኖ መቀጠል ይችላል።” ነበር ያሉት።

በዩናይትድ ስቴትስ፣ ፕሬዝዳንት ባይደን ለእያንዳንዱ ቤተሰብ አራት አራት በአጠቃላይ 5 መቶ ሚልዮን የኮቪድ መመርመሪያዎችን ለዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪዎች ለማድረስ የያዙት ዕቅድ “ጥቁር አሜሪካውያን እና አንዳንድ በወረሽኙ ክፉኛ የተጠቁ ማሕበረሰብ አባላትን ጥቅም በተለይ ሊያጓድል ይችላል” መባሉን ጠቅሶ የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘግቧል።

የጆንስ ሆፕኪንስ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል ዛሬ ማለዳ ላይ እንደዘገበው ቁጥሩ 412 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ በዓለም ዙሪያ ለወረሽኙ ሲጋለጥ፣ የሟቾች ቁጥር 6 ሚሊዮን ደርሷል።

እስካሁን ከ10 ቢሊዮን በላይ ክትባቶች በዓለም ዙሪያ መሰጠቱንም ከማዕከሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

XS
SM
MD
LG