በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በአሜሪካ ከሚገኘው 7 ቢሊየን ዶላር የአፍጋኒስታን ገንዘብ ግማሹ ለ9/11 ተጎጂዎች እንዲሰጥ ሊያደርጉ ነው


Biden Keeping Half of Afghanistan’s $7B in Assets for 9/11 Victims
Biden Keeping Half of Afghanistan’s $7B in Assets for 9/11 Victims

እ.አ.አ በመስከረም 2001 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ በደረሰው የሽብር ጥቃት ተጎጂ የሆኑ ቤተሰቦች የካሳ ጥያቄን ተከትሎ የባይደን አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ ታግዶ ከተቀመጠው የአፍጋኒስታን ማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ 7 ቢሊየን ዶላር ገንዘብ ላይ ግማሹን ለማስቀረት መወሰኑን ታሊባንና የሽብር ጥቃቱ ተጎጂዎች አውግዘዋል።


ባለፈው አመት ነሐሴ ወር ላይ የታሊባን ቡድን ስልጣን ከተቆጣጠረ ወዲህ የምዕራብ ሀገራት በውጪ የተቀመጡ የአፍጋኒስታን እሴቶችንና እና ዓለም አቀፍ ርዳታዎች ማገዳቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚታየው ሰብዓዊ ቀውስ ተባብሷል።

የዩናትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አርብ እለት በፈረሙት ውሳኔ ከዚሁ በዩናይትድ ስቴትስ ታግዶ ከተቀመጠው ገንዘብ ግማሹ ለሀገሪቱ የሰብዓዊ ርዳታ እንዲውል የወሰኑ ሲሆን ቀሪው 3.5 ቢሊየን ዶላር ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድቤቶች እያዩዋቸው ለሚገኙት፣ ታሊባን በ2001 ላደረሰው ጥቃት የካሳ ጥያቄዎች እንዲውል አዘዋል።

ውሳኔውን ተከትሎ የታሊባን ቃል አቀባይ መሀመድ ናኢም በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ "ዩናይትድ ስቴትስ የአፍጋኒስታንን ህዝብ ገንዘብ በመዝረፍ ያሳየችው በሞራልም በሰብዓዊነትም የወረደ ተግባር ነው" ብለዋል።

የባይደን አስተዳደር 3.5 ቢሊየን ዶላሩን በአፍጋኒስታን ለሚደረገው የሰብዓዊ ርዳታ በምን መልኩ እንዲደርስ እንደሚያደርጉ እስካሁን በግልፅ አልተቀመጠም።

XS
SM
MD
LG