በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራሽያ ዩክሬንን በማንኛውም ሰዓት ልታጠቃ ትችላለች ሲሉ ባይደን አስጠነቀቁ


US Australia Quad
US Australia Quad


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ በፊጂ በሚያደርጉት ጉብኝት ዩናይትድ ስቴትስ በሰለሞን ደሴቶች ላይ በድጋሚ ኤምባሲዋን ለመክፈት ያላትን እቅድ የሚያሳውቅ የድህረገፅ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ተገለፀ። ይህም የባይደን አስተዳደር በእስያ ፓስፊክ ቀጠና ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል።


በድህረገፅ አማካኝነት ከቀጠናው መሪዎች ጋር በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ባይደን፣ የዓየር ንብረት ለውጥ ችግር፣ ኮቪድ 19 ወረርሽኝን መግታት፣ የአደጋ ግዜ እርዳታዎች አንድ በፓሲፊክ ሀገራት ዲሞክራሲ እና አንድነት ሊሰፍን በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ቻይና ከቀጠናው ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት እያደረገች ባለችበት ወቅት መሆኑም ተገልጿል። ረዳት

ብሊንከን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ወደ አውስትራሊያ አቅንተው፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ አውስትራሊያ፣ ጃፓን እና ህንድን ጨምሮ ከያዘው የኩዋድ አገራት መሪዎች ጋር ተገናኝተው የነበረ ሲሆን፣ አርብ እለት ባወጡት የጋራ መግለጫ የህንድ-ፓስፊክ አካባቢን ከማንኛውም ጫና ነፃ ለማድረግ የጋራ ትብብር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። ይህም የቻይናን የኢኮኖሚና ወታደራዊ መስፋፋት የሚያመለክት ነው ተብሏል።

ስብሰባውን ያስተናገዱት የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሪዝ ፓይን እንደተናገሩት፣ የኩዋድ መሪዎች ስብሰባ በቀጠናው የሚኖረው የፀጥታ ጉዳይ ዩናይትድ ስቴትስ ትኩረት የምትሰጠው ጉዳይ ሆኖ እንደሚቀጥል ለቻይና መልዕክት ያስተላልፋል ብለዋል።

የባይደን ጉብኝትም አስተዳደራቸው በእስያ-ፓስፊክ ቀጠና የሚሰጠው ትኩረት እንደቀጠለ መሆኑንና በዩክሬን ያለው ችግር ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች እንደማያደናቅፈው ለማሳየት መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG