ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላ ዓለም የሚኖሩ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለምግብነት ከሚያውሏቸው አዝዕርት መካከል አንዱ ማሽላ ነው። ማሽላን በማጥቃት ፍሬ እንዳይሰጥ ከሚያደርጉት በሽታዎች መካከል አንዱ ደግሞ “አንትራክኖስ “ ይባላል።
በቅርቡ በውጭ ሀገር እና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ተመራማሪዎች ተባብረው ይሄንን ከሻጋታ የሚመነጭ ጸረ ተክል-የሚመክት መላ አግኝተዋል።
የምርምር ቡድኑን የመሩት ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ኢንዲያና ግዛት በሚገኘው ፐርዱ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመምህርነት እያገለገሉ ያሉት ፕሮፌሰር ተስፋዬ መንግስቴ ናቸው ። ሀብታሙ ስዩም ከሳቸው ጋር ያደረገውን ቆይታ በመቀጠል ያሰማናል።