ድሬዳዋ —
የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ ከሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድርቅ ምክንያት ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ጎብኝተዋል።
ከቀያቸው ተፈናቅለው “ፋፈን” የተሰኘ ዞን የሚገኙ የድርቅ ተጎጂዎችን በስፍራው ተገኝተው ያነጋገሩ ሲሆን ጊዜያዊና ዘላቂ ያሏቸውን መፍትሔዎችንም ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ለተጎጂዎቹ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ምስራቅ አፍሪካን እየጎዳው ባለው ድርቅ ሳቢያ የተቸገሩ ሶማሊያውያን ከሃገራቸው ተሰድደው ወደ ሶማሌ ክልል መግባት መጀመራቸውን የሶማሌ ክልል አስታውቋል።
ክልሉ አሁን ካለበት ጫና እንዲሁም የስደተኞችን መግባት ተከትሎ ከሚፈጠረው የጸጥታ ሥጋት አንጻር ሶማሊያውያኑ ባሉበት እርዳታ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች የሶማሌ ክልል የተባበሩት መንግሥታትን ጠይቋል።