በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ውስጥ በነዳጅ ማከማቻ መርከብ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ


ፎቶ ፋይል፦ /FPSO Trinity Spirit/ የተባለችው እና በናዳጅ ማምንጨት ሥራ የተሰማራችው መርከብ
ፎቶ ፋይል፦ /FPSO Trinity Spirit/ የተባለችው እና በናዳጅ ማምንጨት ሥራ የተሰማራችው መርከብ

ባለፈው ሳምንት በናይጄሪያ በአንዲት ነዳጅ ማከማቻ መርከብ ላይ በደረሰው ፍንዳታ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ኩባንያው አስታወቀ።

/FPSO Trinity Spirit/ የተባለችው እና በናዳጅ ማምንጨት ሥራ ጭምር የተሰማራችው ይህች መርከብ በደረሰባት አደጋ ወቅት በሥራ ላይ የነበሩ ሌሎች አራት የመርከቢቱ ሠራተኞችም የገቡበት ያለመታወቁን ኩባንያው ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የናይጄሪያው ሼባህ የነዳጅ ፍለጋ እና አምራች ኩባንያ (SEPCOL) ጨምሮም ባለፈው ረቡዕ ፍንዳታው በደረሰው ወቅት መርከቢቱ ላይ አሥር ሰራተኞቿ እንደነበሩ እና ሶስቱ ባለፈው ሳምንት በህይወት ሲገኙ፤ ትናንት እሁድ ደግሞ ሌሎች ሦስት ሰዎች ሞተው መገኘታቸውን አስታውቋል።

"ቅድሚያ ትኩረታችን አሁንም እስካሁን የገቡበት ያልታወቁትን አራቱን የመርከቢቱ ሰራተኞች ፈልጎ ማግኘት እና ደህንነታቸውን ማረጋገጥ ነው" ብሏል ኩባንያው።

የነዳጅ ማመንጨት፣ ማከማቻ እና ማራገፍ ሥራ የምታከናውነው መርከብ በፍንዳታው ወቅት ነዳጅ በማውጣት ሥራ ላይ እንዳልነበረች ታውቋል።

XS
SM
MD
LG