በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብራዚል ውስጥ የኮንጎሌዝ ስደተኛ መገደል ቁጣ አስነሳ


የ24 ዓመቱ ስደተኛ ሟሴ ሙጌንዪ ካባጋምቤ ሪዮ ግድያተከትሎ በመላ ሃገሪቱ ቁጣ ቁጣ ተነስቷል/Feb. 5, 2022/
የ24 ዓመቱ ስደተኛ ሟሴ ሙጌንዪ ካባጋምቤ ሪዮ ግድያተከትሎ በመላ ሃገሪቱ ቁጣ ቁጣ ተነስቷል/Feb. 5, 2022/

አንድ ኮንጎሌዛዊ ስደተኛ ሰሞኑን ብራዚል ውስጥ ተደብድቦ ከተገደለ በኋላ የሃገሪቱ ግዙፍ ከተሞች በተቃውሞ ሰልፎች መጨናነቃቸውን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የ24 ዓመቱ ስደተኛ ሟሴ ሙጌንዪ ካባጋምቤ ሪዮ ዴ ጃኔይሮ ውስጥ ባራ ዳ ቲህዋካ በሚባል የመኖሪያና የገበያ አካባቢ አንድ ኪዮስክ ውስጥ ይሠራ የነበረ ሲሆን ማንነታቸው ባልተገለፀ ሰዎች ተደብድቦ የተገደለው ባለፈው ጥር 16 /የዛሬ ሁለት ሣምንት አካባቢ/ ነበር።

ሟሴ ይሠራበት ወደነበረ ሱቅ የሚወስድ መንገድ ዛሬ በሁለት መሥመር በቆሙ ሰልፈኞች መሞላቱና ፎቶዎቹና የሟሴን ገፅታ በያዙ ሥዕሎች፣ እንዲሁም በባነሮችና ፅሁፎች መሸፈኑ ተነግሯል።

ግድያውን ተከትሎ በመላ ሃገሪቱ ቁጣ ከተነሳ በኋላ ትናንት እና ዛሬ ሪዮ፣ ሳዖ ፖሎና ሌሎችም ግዙፍ ከተሞች ውስጥ ከፍተኛ ሰልፎች መደረጋቸው ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG