በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በቀድሞ ባለሥልጣናቱ ዋስትና ጉዳይ


የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት

ቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸዉ አሰፋ መዝገብ ከተከሰሱት ሰዎች መካከል ሃያዎቹ በዋስ እንዲፈቱ የተወሰነው ረዘም ላለ ጊዜ በተካሄደ የፍርድ ቤት ሂደትና ክርክር እንጂ በፖለቲካዊ ውሳኔ አለመሆኑን ከተከሳሾቹ ጠበቆች አንዱ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።

የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡት ሕዳር 30 እንደነበረም ጠበቃዉ አቶ ዮሴፍ ኪሮሰ አስረድተዋል።

"የፖለቲካ ውሳኔ ቢሆን ኖሮ አቃቤ ሕግ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የዋስትና መብት አይቃወምም ነበር።" በማለትም አብራርተዋል።

ዓቃቤ ሕግ ያቀረበዉን ይግባኝ መነሻ አድርጎ ትናንት የሁለቱን ወገኖች ክርክር ያዳመጠው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 7/2014 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱንም አቶ ዮሴፍ ተናግረዋል።

ሰሞኑን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የፍትህ ሚኒስትር ዲኤታ ፈቃዱ ፀጋ የዋስትና ውሳኔዉ በቅርቡ መንግሥት ይፋ ካደረጋቸዉ ክስ የማቋረጥ እረምጃዎች ጋር የማይገናኝና ይግባኝ የተጠየቀበት መሆኑን አስታውቀዋል።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በቀድሞ ባለሥልጣናቱ ዋስትና ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:40 0:00


XS
SM
MD
LG