በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በወሰደችው የአጸፋ እምርጃ የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያን ዘጋች


የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ (ዶቸ ዌሌ)
የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ (ዶቸ ዌሌ)

ሩሲያ ዛሬ ሀሙስ ባወጣችው መግለጫ ጀርመን ለወሰደችው አጸፋ በሞስኮ የሚገኘውን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ፣ ዶቸ ዌሌን መዝጋቷን አስታወቀች፡፡

ሩሲያ የአጸፋውን እርምጃ የወሰደቸው የጀርመን መንግሥት አርቲ ደ (RT DE) በተሰኘው የሩሲያ ራዲዮ ጣቢያ ላይ የወሰደችውን እምርጃ ተከትሎ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ ለዶቸ ዌሌ የሩሲያ ቢሮ ሠራተኞ በሙሉ የተሰጠው ፈቃድ መሰረዙንና በሩሲያ ግዛት የሚደረገው የጣቢያው ስርጭት እንዲቆም መደረጉን አስታውቋል፡፡

በጀርመንየመገናኛ ብዙሃንን የሚቆጣጠረው አካል የሩሲያን ሚዲያ ያገደው ፣ በጀርመን የሚንቀሳቀሰው የሩሲያው የ'አርቲ ደ' ሬዲዮ በሳይቤሪያ ፈቃድ ማሰራጨት የማይችል መሆኑን በመግለጽ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG