በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ጦር በሶሪያ የተሳካ የጸረ ሽብር ተልእኮ ፈጽሜያለሁ አለ


የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ጥር 26፣ 2014 ዓ.ም በሲሪያ እድሊብ ከተማ ላይ ባካሄደው ጥቃት ይወደሙ ቤቶች
የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ጥር 26፣ 2014 ዓ.ም በሲሪያ እድሊብ ከተማ ላይ ባካሄደው ጥቃት ይወደሙ ቤቶች

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታገን) ዛሬ ሀሙስ ባወጣው መግለጫ በልዩ ኃይሉ አማካይነት በሶሪያ ምስራቃዊ ግዛት ባደረሰው ጥቃት የተሳካ የጸረ ሽብር ተልእኮውን መወጣቱን አስታውቋል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የፔንታገን ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ በተልእኮው በዩናይትድስቴትስ በኩል የደረሰ ጉዳት አለመሩንና ዝርዝሩ ወደፊት በሠራዊቱ በኩል እንደሚገለጽ ከመናገራቸው ውጭ ተጨማሪ መረጃ አልሰጡም፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ለሁለት ሰዓታት ያህል በቆየው ውጊያ፣ ሂሊኮፕተሮች የተሳተፉበት ተኩስና ፍንዳታዎች የተሰሙበት ሲሆን በርካታ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡

በምሽት የተከናወነው ድንገተኛ ጥቃት የተካሄደው በቱርክ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘውና የሶሪያ አማጽያን የመጨረሻዋ ይዞታ በሆነቸው እድሊብ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ አካባቢው ከአልቃይዳ ጀምሮ እስከተለያዩ የሚሊሻ ቡድኖች ድረስ የሚቀንሳቀሱበት ስፍራ መሆኑም ተነገሯል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ኃይል እኤአ በ2019 የቀድሞ የእስላማዊ መሪ አቡ ባካር አልባግዳዲን የገደለው በዚህ ስፍራ መሆኑም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG