በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የኔቶን ጦር ለማጠንከር ተጨማሪ ወታደሮች መላኳን ዋና ጸሀፊው አደነቁ


ፋይል: የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች እ.አ.አ በጥር 12፣ 2017 ዓ.ም. ምዕራብ ፖላንድ በሚገነው ዣጋን የጦር ሰፈር ሲደርሱ
ፋይል: የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች እ.አ.አ በጥር 12፣ 2017 ዓ.ም. ምዕራብ ፖላንድ በሚገነው ዣጋን የጦር ሰፈር ሲደርሱ

የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄን ስቶልተንበርግ፣ ዛሬ ሀሙስ በሰጡት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ አውሮፓ ለማሰማራት ማቀዷን አድንቀዋል፡፡ ኔቶም ተጨማሪ ተዋጊ ወታደሮችን የቃል ኪዳን አገሮቹ ወታደሮች በሚገኙበትና፣ የሩሲያና ዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ወዳለው ደቡባዊ ምስራቅ አካባቢ ለማሰማራት፣ ማቀዱን አስታውቀዋል፡፡

ዋና ጸሀፊው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫቸው፣ በኔቶም በኩል ፣ ሩሲያ ወታደራዊ እርምጃ ከወሰደች በሚል የሚደረግ ዝግጅት መኖሩን ጠቅሰው፣ በሌላ በኩልም ትርጉም ባለው ንግግር ለመሳተፍና ለቀውሱ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለመስጠት ኔቶ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“ኔቶ ሩሲያ ውጥረቱን እንድታረግብ ማሳሰቡን ይቀጥላል፡፡” ያሉት ዋና ጸሀፊው ፣ ከዚህ ያለፈ የትኛውም የሩሲያ እምርጃ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፣ ትልቅ ዋጋም ያስከፍላል” ብለዋል፡፡

በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ 100ሺ ጦር አሰልፋለች ስለተባለችውም ሩሲያም ሲናገሩ “ይህ ሩሲያ ከሁለተኛው አለም ጦርነት ወዲህ ያሰማራችው ትልቁ ጦር ነው” ብለዋል፡፡

ዩናይትድስቴትስ ቀደም ሲል እልከዋለሁ ካለቸው 8ሺ 500 ጦር በተጨማሪ፣ በትናንትናው እለት፣ 2ሺ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ አውሮፓ የምትልክ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ወደ ፖላንድ እንደሚሄዱና፣ ጀርመን ከሚገኘው ጦሯ የኔቶ ጦርን ለማጠናከር አንድ ሺ ወታደሮችን ለመላክ መወሰኗንም አስታውቃለች፡፡

የክሬምሊን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ዲምፕትሪ ፔስኮቭ፣ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ዩናይትድ ስቴትስ ወደ አካባቢው የምትልከው ጦር በአካባቢው ያለውን ውጥረት ያባብሳል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG