በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሆስፒታል የገቡት ዴሞክራቱ የምክር ቤት አባል ለባይደን አጀንዳ ስጋት ሆነዋል


ዴሞክራቱ የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባል ሴናተር ቤን ሬይ
ዴሞክራቱ የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባል ሴናተር ቤን ሬይ

በልብ ድካም ህመም ድንገት ሆስፒታል የገቡት ዴሞክራቱ የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባል አገግመው ሊወጡ መቻላቸው ቢነገርም፣ ወደ ምክርቤቱ እስኪመለሱ ድረስ፣ በቋፍ ያለው የዴሞክራቶች አጀንዳ ታግቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑ ተነገረ፡፡

የ49 ዓመቱ ሴናተር ቤን ሬይ ባላፈውሳምንት መጨረሻ ከተደረገላቸው የጭንቅላት የቀዶ ጥገና ወጥተው እዚያ ሆስፒታል ውስጥ እያገገሙ መሆኑ ሲነገር፣ ወደ ሥራ ሊመለሱ የሚችሉት ሁሉም ነገር ሰላም ከሆነ፣ ከዛሬ አራትና ስድስት ሳምንታት በኋላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የምክር ቤት አባል ድምጽ መስጠት ያለበት በአካል ቀርቦ ብቻ በመሆኑ፣ በዴሞክራቶችና ሪፐብሊካን 50 ለ50 በተከፈለው ምክርቤት፣ በምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ ይገኝየነበረው ተጨማሪ ድምጽ፣ ወሳኝ የማይሆንበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ተገምቷል፡፡

የዋይት ሀውስን ትላልቅ አጀንዳዎች የሚያራምዱት ዴሞክራቶቹ የምክር ቤት መሪዎች፣ስጋት የገባቸው ሲሆን ትላልቅ የበጀት ረቂቅ ህጎችና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመትየመሳሰሉት የፕሬዚዳንት ባይደን አጀንዳዎች በምክር ቤቱ ከፍተኛ ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል የአጃንስ ፍራንስ ፕሬዚስ ዘገባ አመልከቷል፡፡

XS
SM
MD
LG