በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን 6 ቢሊዮን ብር መገኘቱን ክልሉ አስታወቀ


በአማራ ክልል የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን 6 ቢሊዮን ብር መገኘቱን ክልሉ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:55 0:00

በአማራ ክልል የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን 6 ቢሊዮን ብር መገኘቱን ክልሉ አስታወቀ

በአማራ ክልል በጦርነቱና በጥቃት ምክንያት የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት መልሶ ለማልማትና ድርቅን ለመከላከል ወደ 6 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የእርዳታ ሥምምነት ኤፍኤች ኢትዮጵያ ከተሰኘ ለጋሽ ድርጅት ጋር መፈራረሙን የክልሉ ገንዘብ ቢሮ አስታወቀ።

ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት /UNDP/እና ከህፃናት መርጃ ድርጅት /UNICEF/ በተለያየ እርዳታ ማግኘታቸውንም ዶ/ር ጥላሁን ማህሪ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ 266 ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ውስጥ 28ቱ የፕሮጀክት እቅድ ቀይረው ለተጎዱ ወገኖች የዓይነትና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ዶ/ር ጥላሁን ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ ድርጅቶቹ በአማራ ክልል የደረሰውን ጉዳት እየተረዱ ነው ያሉት ኃላፊው የሚያስፈልገው ግን ከዚህ የበዛ ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG