በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያው የአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ ጊዜያዊ ጉዳይ አስፈፃሚ ተሾመለት


በውጭ ጉዳይ ዘርፍ የረጅም ጊዜ አገልግሎትና ከፍተኛ ልምድ ያላቸው አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን፤ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አዲስ ጊዜያዊ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ጡረታ ለመውጣት በዝግጅት ላይ የሚገኙትን በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ጌታ ፓሲን ተክተው እንዲሰሩ መሾማቸውን ተክተው እንዲሰሩ መሾማቸውን መግለጫው አመልክቷል።

አምባሳደር ትሬሲ አን ቀደም ሲል ኮሶቮ፣ ታጃክስታንና ተርክሚስታን ጨምሮ በተለያዩ አገሮች የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር በመሆን የላቀ አገልግሎታቸውን እንዳከናወኑት ሁሉ በኢትዮጵያም ዩናይትድ ስቴትስ ያላትን ሥራዎች ሁሉ ይመራሉ ሲል መግለጫው አመልክቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ አምባሳደሯ በኢትዮጵያ ያለው ግጭትና እየደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ ያልተገደበ የሰብአዊ ተደራሽነትና አቅርቦት እንዲኖር፣ ያሉት ግጭቶች በሰላማዊ ድርድር እንዲፈቱ ቀደም ሲል በአምባሳደር ፓሲ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መወሰኑን አመልክቷል፡፡

የአሜሪካን እሴቶችጥና ጥቅሞችን በማሳደግ፣ የላቀ የህዝብ አገልግሎት ላበረከቱት ለከፍተኛዋ ዲፕሎማት፣ ለተሰናባቿ አምባሳደር ፓሲ፣ የዩናይትድ ስቴት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትልቅ አክብሮትና አድናቆት ያለው መሆኑንም በመግለጫው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG