በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ጸጥታ ምክር ቤቱ በሩሲያ ጉዳይ ተነጋገረ


ፎቶ ፋይል፡ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶመስ
ፎቶ ፋይል፡ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶመስ

ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ሩሲያ በዩክሬን ድንበር ስላከማቸችው 100ሺ ወታደሮችና እሱንም ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ እንዲነጋገር የጠራቸው ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶመስ ትናንት እሁድ በኤቢሲ ቴሌቪዥን ጣቢያ ምክር ቤቱ ሩሲያን ወታደሮቿችን ያሰፈረችበት ምክንያት አጥብቆ እንደሚጠይቃት ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሯ በንግግራቸው ሩሲያውያን ሁኔታውን ራሳቸው ቀርበው እንዲያብራሩ ሁላችንም በተስማማ ድምጽ ጥሪውን አቅርበናል ብለዋል፡፡

በተባበሩ መንግሥታት የሩሲያ ረዳት አምባሳደር ዲምትሪ ፖሊያንስኪ የስብሰባት የተጠራው ዝምብሎ ለህዝብ ግንኙነት ፍጆታ ነው ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

ሩሲያ ከመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባልና ድምጽም በድምጽ የመሻር ሥልጣን ካላቸው አምስቱ አገሮች አንዷ በመሆንዋ የሚተላለፈውን ውሳኔ ሁሉ መሻት የምትችል መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG