በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቶዮታ ጨረቃ ላይ የሚነዳ ሉና ክሩዘር የተባለ ተሽከርካሪ ሊሰራ ነው


በቶዮታ ሞተር ኮርፖሬሽን የቀረበው የጠፈርን የውስጥና ውጭ ከባቢን ከሚመረምረው የጃፓን ተቋም ጋር ይሠራል የተባለው የቶዮታው የጠፈር ላይ ተሽከርካሪ፣ ሉና ክሩዘር
በቶዮታ ሞተር ኮርፖሬሽን የቀረበው የጠፈርን የውስጥና ውጭ ከባቢን ከሚመረምረው የጃፓን ተቋም ጋር ይሠራል የተባለው የቶዮታው የጠፈር ላይ ተሽከርካሪ፣ ሉና ክሩዘር

ተሽከርካሪ አምራቹ ኩባንያ ቶዮታ፣ ከጃፓን የጠፈር ምርምር ተቋም ጋር በመተባበር የጠፈርና ጨረቃ ላይ ተሽከርካሪ ለመስራት ምርምር እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ዓላማው እኤአ በ2040 ጨረቃ ላይ እንዲሁም ወደፊት ማርስ ላይ መኖር የሚፈልጉ ሰዎችን ህልም ለማሟላት ነው ተብሏል፡፡

በሚደረገው የጨረቃ ገጽታ ምርምር ላይም ቶዮታ ተሽክርካሪዎችን በማቅረብ ተሳታፊ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡

የጠፈርን የውስጥና ውጭ ከባቢን ከሚመረምረው የጃፓን ተቋም ጋር ይሠራል የተባለው የቶዮታው የጠፈር ላይ ተሽከርካሪ፣ ሉና ክሩዘር ተብሎ እንደሚጠራ ተገልጿል፡፡

ሉና ክሩዘር በምድር ላይ ቶዮታ ላንድ ክሩዘር ከተሰኘው መጠሪያ ጋር የተዛመደ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

በቶዮታ የፕሮጀክቱ ኃላፊ ታኮ ሳቶ ለአሶሼይትድ ፕሬስ እንደተናገሩት ጠፈርን የምናየው በመቶ ዓመት አንዴ እንደሚመጣ አጋጣሚ አድርገን ነው ብለዋል፡፡

ለጠፈር ተማራማሪዎች አደጋን ሊደቅን በሚችለው ጠፈርም አጋዥ የሚሆኑ ሮቦቶች እንደሚሰሩም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG